የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ ዝርዝር ጥናት እና አማራጭ የግንባታ አተገባበርና የልደታ ተ/ሃይማኖት ሳይት የዋጋ ጥናት - ክፍል አንድ

የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ ዝርዝር ጥናት እና አማራጭ የግንባታ አተገባበርና የልደታ ተ/ሃይማኖት ሳይት የዋጋ ጥናት - ክፍል አንድ

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ ዝርዝር ጥናት እና አማራጭ የግንባታ አተገባበርና የልደታ ተ/ሃይማኖት ሳይት የዋጋ ጥናት


ረቂቅ 




•ኮንስትክሽን በሀገራችን በስፋት እያደጉ ካሉ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ በተለይ ደሞ በመንገድ እና በህንፃ ግንባታ ዘርፍ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይቶአል፡፡
•በህንፃ ግንባታ ዘርፍ በተለይም በሪል እስቴት ዘርፍ በግል ባለሀብቶች እንዲሁም በመንግስት መጠነ ሰፊ መዋለ ነዋይ በማፍሰስ በሰፊው እየተሰራ ይገኛል፡፡
•በከተማው ውስጥ ያለው የቤት እጥረት ለመቅረፍ በመንግስትም ሆነ በግል  ባለሃብቱ ዘንድ ብዙ እንቅስቃሴ ቢደረግም ፍላጎትን እና አቅርቦን በማቀራረብ ያለውን ችግር ለመፍታት አልተቻለም፡፡ 
በምክኒያትነት የሚጠቀሱ ብዙ ጉዳዮች ቢኖሩም በዋነኛነት የሚጠቀሱት 
የገንዘብ ( የበጀት እና  የዋጋ ንረት)
የጊዜ ( ፕሮጀክትን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሚወስደው ) 
የጥራት (ግንባውን በሚፈለገው እና በተቀመጠለት መስፈርት መስራት) ዋነኞቹ ናቸው፡፡
የዚህ ጥናት ዋነኛ አላማ ይህን ችግር መቅረፍ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ እየተሰራበት የሚገኝ እና ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መቅረፍ የሚያስችል አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂ አቅርበናል፡፡ 

•ይህ ቴክኖሎጂ አልሙኒየም ፎርም ወርክ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በአለማችን ላይ በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተሰራበት ይገኛል፡፡የጊዜን እና የጥራትን ጉዳይ በሚመለከት ወደር የማይገኝለት መፍትሄ ሲሆን በተለይም መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮጀክትን እና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ የገንዘብና የግብአትን ብክነትን የሚያስወግድ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
•አልሙኒየም ፎርም ወርክ  ከቤቶች ልማት (mass housing )በአጭር የግንባታ ጊዜ በትንሽ የሰው ሃይልና በአነስተኛ ዋጋ ፕሮጀክቶችን መከወን የሚያስችል የግንባታ ቴክኖሎጂ ነው፡፡